Wednesday, October 20, 2010

እንኳን ወደ "ቤት ለእንግዳ Baga Nagaan Dhuftan" የጡመራ ዓምድ መጡ


ሰላም...!
የከበረ ሰላምታዬ በያላችሁበት ይድረሳችሁ፡፡ ይህ በዛሬው ዕለት የምጀምረው የጡመራ መድረክ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዶግማ፣ ቀኖና እና ትውፊት መሠረት ከእናንተ ጋር የምገናኝበት መድረክ ነው፡፡ በዚህ ዓምድ እግዚአብሔር እንደፈቀደ መጠን በነገረ ሃይማኖት ዙርያ ያሉኝን መረጃዎች ለጎብኚዎቼ ለማጋራት እጥራለሁ፡፡ አቅሜ በፈቀደ መጠን በአማርኛ እና በኦሮምኛ ቋንቋ ሳነብ ያገኘኋቸውን፤ በትምህርት ከቅድስት ቤተክርስቲያን የቀሰምኩትን ለማስተላለፍ ብርቱ ጥረት አደርጋለሁ፡፡ አልፎ አልፎም በልሳነ ግዕዝ፣ በልሳነ ትግርኛ እና እንግሊዝኛ የተጻፉ መረጃዎችን እንደሁኔታው አመቺነት በዚህ ብሎግ ለንባብ ይቀርባሉ፡፡

“የያዘውን የወረወረ…” እንዲሉ እኔ ያለኝን ለማሳተፍ ዝግጁ ስሆን የእናንተ ጸሎትና አስተያየት እንዳይለየኝ እማጸናለሁ፡፡ ያነሳሳን እግዚአብሔር ዘወትር በረድኤት አይለየን፡፡ የወላዲተ አምላክ ምልጃና ጸሎት የቅዱሳን አማላጅነት ከእኛ ጋራ ይሁን፡፡ አሜን፡፡