ቤት ለእንግዳ: ጫካው ለዛፎች ብቻ (ከዲያቆን ዳንኤል ድረ-ገጽ የተገለበጠ)
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይጠብቅ! አሜን።
ቤት ለእንግዳ Baga Nagaan Dhuftan
Saturday, November 26, 2011
Friday, October 7, 2011
ዜና ቅድስት ደብረ ገነት ዘዊኒፔግ Zena Debre Genet Ze Winnipeg: ዘመነ ጽጌ - በዲ/ን ዳንኤል ክብረት / Zemene Tsige D/n Daniel ...
ዜና ቅድስት ደብረ ገነት ዘዊኒፔግ Zena Debre Genet Ze Winnipeg: ዘመነ ጽጌ - በዲ/ን ዳንኤል ክብረት / Zemene Tsige D/n Daniel ...: ዘመነ ጽጌ - በዲ/ን ዳንኤል ክብረት Zemene Tsige D/n Daniel Kibret
Si Jaalanna
Si jaalanna Mariyaam hadha kenyaa (፪)
Ijaa nuu deesseef nyaata lubbu keenyaa
Maariyaam baay’e sijaalanna
Cubbudhaan kufukoo Yaa Maariyaam
Ati hin ilaalinii Yaa Maariyaam
Abdiin koo sumadha Yaa Maariyaam
Nan ka’a kadhaa keen Yaa Maariyaam
Siittan himadhaa Yaa Maariyaam
Waan jirynay koo Yaa Maariyaam
Ijaa naaf taateef Yaa Maariyaam
Wabii gaafa rakkoo Yaa Maariyaam
Ceesisa…
Miidhaga amantootaa Yaa Maariyaam
Kan qulqullooftee Yaa Maariyaam
Lubbuu nama gadde Yaa Maariyaam
Baay’e gammachiftee Yaa Maariyaam
Cubbu dhaan kan kufe Yaa Maariyaam
Kaafte jabeessite Yaa Maariyaam
Maqaakee kan waamef Yaa Maariyaam
Kennaakee uffistee Yaa Maariyaam
Ceesisa…
Maqaankee guddaadha Yaa Maariyaam
Nama yaadateefi Yaa Maariyaam
Abdi namaaf ta’a Yaa Maariyaam
Nama qabateefi Yaa Maariyaam
Jireenyakoo hundaa Yaa Maariyaam
Calala naaf godhi Yaa Maariyaam
Garakettan iyyaa Yaa Maariyaam
Kadhaakoo dhagayii Yaa Maariyaam
Ceesisa….
ማርያም እንወድሻለን በሚለው መዝሙር ዜማ የሚዘመር የኦሮምኛ መዝሙር
ውዳሴ ማርያም እጮኸለሁደንግል እናቴን እጣራለሁእንደ አባ ኤፍሬም ነይ ባርኪኝወድሰኒ ልጄ በይኝ
በሠርክ ጸሎት ላይ ውዳሴ ማርያም
ዜማ ስናደርስ ውዳሴ ማርያም
ድንግል ትመጣለች ውዳሴ ማርያም
በቤተ መቅደስ ውዳሴ ማርያም
የብርሃን ምንጣፍ ውዳሴ ማርያም
ከፊቷ ተነጥፏል ውዳሴ ማርያም
ቅዱስ ኤፍሬም ታጥቆ ውዳሴ ማርያም
ያመሰግናታል ውዳሴ ማርያም
አዝ..
አባ ሕርያቆስም ውዳሴ ማርያም
ምሥጋና ያደርሳል ውዳሴ ማርያም
የቅዳሴው ዜማ ውዳሴ ማርያም
ልብን ይመሰጣል ውሳሴ ማርያም
በጎ ነገር ልቤ ውዳሴ ማርያም
አወጣ እያለ ውዳሴ ማርያም
ዳዊት በገናውን ውዳሴ ማርያም
እየደረደረ ውዳሴ ማርያም
አዝ...
የንጽሕናችንን ውዳሴ ማርያም
መሠረት ነሽና ውዳሴ ማርያም
አንቺን ለማመስገን ውዳሴ ማርያም
ልቡናዬ ይብራ ውዳሴ ማርያም
ተፈሥሒ ደንገል ውዳሴ ማርያም
ኦ ቤተልሔም ውዳሴ ማርያም
ከአንቺ ተወለደ ውዳሴ ማርያም
መድኃኔዓለም ውዳሴ ማርያም
አዝ...
ቅዱሳኑ ሁሉ ውዳሴ ማርያም
ዙሪያሽን ከበዋል ውዳሴ ማርያም
አባ ጊዮርጊስም ውዳሴ ማርያም
ንኢ ድንግል ይላል ውዳሴ ማርያም
በወርቅ ዙፋን ለይ ውዳሴ ማርያም
ተቀምጠሸ ሳይሽ ውዳሴ ማርያም
ልቤ ተሰወረ ውዳሴ ማርያም
ድንግል ተሰወረ ውዳሴ ማርያም
ደንግል በግርማሽ ውዳሴ ማርያም
Tuesday, September 13, 2011
የዘመናት ጌታ
የዕለት የዓመት
የዕለት የዓመት የዘመናቱ ጌታ
ለዚህ ላደረስከኝ ዘመኔን ሳትገታ
አቀርብልሃለሁ የክብር ሰላምታ /፪/
ኑ እናመስግን ከልባችን
የሰማዩን አባታችንን
ከዚህ ዕለት ከዚህ ዓመት ላደረሰን ሁላችንን
የሰው ልጆች ዕድሜ ጥንቱንም ሲጀመር
ምን ቢወጣ ቢወርድ ቢበዛ ቢደመር
አንድ ቀን አይሞላም እንዳንተ አቆጣጠር /፪/
አዝ…
ስለዚህ አምላክ ሆይ ክቡር ነው ቅዱስ ነው
ወዳንተ እንዲመለስ ቀን የሰጠኸው ሰው
ደካማ ነውና ሰው ዕድሜ ከራበው /፪/
አዝ…
እጅግ አደንቃለሁ የአምላክን ጥበብ
ምድርን በአበባ ሰማዩን በኮከብ
እንዳሸበረቃት አስተውዬ ሳስብ /፪/
አዝ…
በከንቱ ጊዜአችን ፈጽሞ እንዳይጠፋ
በርትተን ከሠራን ያላንዳች ነቀፋ
አምላክ የሚሰጠን አለን ፍጹም ተስፋ /፪/
አዝ…
ከንቱ ካሳለፍኩት ጊዜዬን በዋዛ
ምን ያደርግልኛል ዘመኔ ቢበዛ
ደግሞም በጠቅላላው ዓለምን ብገዛ /፪/
አዝ…
ወርሃ ክረምት አልፎ መስከረም ሲጠባ
ምድር በልምላሜ ስታጌጥ በአበባ
እናምናለን ላንተ ምስጋና እንዲገባ /፪/
Wednesday, October 20, 2010
እንኳን ወደ "ቤት ለእንግዳ Baga Nagaan Dhuftan" የጡመራ ዓምድ መጡ
ሰላም...!
የከበረ ሰላምታዬ በያላችሁበት ይድረሳችሁ፡፡ ይህ በዛሬው ዕለት የምጀምረው የጡመራ መድረክ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዶግማ፣ ቀኖና እና ትውፊት መሠረት ከእናንተ ጋር የምገናኝበት መድረክ ነው፡፡ በዚህ ዓምድ እግዚአብሔር እንደፈቀደ መጠን በነገረ ሃይማኖት ዙርያ ያሉኝን መረጃዎች ለጎብኚዎቼ ለማጋራት እጥራለሁ፡፡ አቅሜ በፈቀደ መጠን በአማርኛ እና በኦሮምኛ ቋንቋ ሳነብ ያገኘኋቸውን፤ በትምህርት ከቅድስት ቤተክርስቲያን የቀሰምኩትን ለማስተላለፍ ብርቱ ጥረት አደርጋለሁ፡፡ አልፎ አልፎም በልሳነ ግዕዝ፣ በልሳነ ትግርኛ እና እንግሊዝኛ የተጻፉ መረጃዎችን እንደሁኔታው አመቺነት በዚህ ብሎግ ለንባብ ይቀርባሉ፡፡ “የያዘውን የወረወረ…” እንዲሉ እኔ ያለኝን ለማሳተፍ ዝግጁ ስሆን የእናንተ ጸሎትና አስተያየት እንዳይለየኝ እማጸናለሁ፡፡ ያነሳሳን እግዚአብሔር ዘወትር በረድኤት አይለየን፡፡ የወላዲተ አምላክ ምልጃና ጸሎት የቅዱሳን አማላጅነት ከእኛ ጋራ ይሁን፡፡ አሜን፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)