የዕለት የዓመት
የዕለት የዓመት የዘመናቱ ጌታ
ለዚህ ላደረስከኝ ዘመኔን ሳትገታ
አቀርብልሃለሁ የክብር ሰላምታ /፪/
ኑ እናመስግን ከልባችን
የሰማዩን አባታችንን
ከዚህ ዕለት ከዚህ ዓመት ላደረሰን ሁላችንን
የሰው ልጆች ዕድሜ ጥንቱንም ሲጀመር
ምን ቢወጣ ቢወርድ ቢበዛ ቢደመር
አንድ ቀን አይሞላም እንዳንተ አቆጣጠር /፪/
አዝ…
ስለዚህ አምላክ ሆይ ክቡር ነው ቅዱስ ነው
ወዳንተ እንዲመለስ ቀን የሰጠኸው ሰው
ደካማ ነውና ሰው ዕድሜ ከራበው /፪/
አዝ…
እጅግ አደንቃለሁ የአምላክን ጥበብ
ምድርን በአበባ ሰማዩን በኮከብ
እንዳሸበረቃት አስተውዬ ሳስብ /፪/
አዝ…
በከንቱ ጊዜአችን ፈጽሞ እንዳይጠፋ
በርትተን ከሠራን ያላንዳች ነቀፋ
አምላክ የሚሰጠን አለን ፍጹም ተስፋ /፪/
አዝ…
ከንቱ ካሳለፍኩት ጊዜዬን በዋዛ
ምን ያደርግልኛል ዘመኔ ቢበዛ
ደግሞም በጠቅላላው ዓለምን ብገዛ /፪/
አዝ…
ወርሃ ክረምት አልፎ መስከረም ሲጠባ
ምድር በልምላሜ ስታጌጥ በአበባ
እናምናለን ላንተ ምስጋና እንዲገባ /፪/
No comments:
Post a Comment